"አገር ለማፍረስ ከህወሓት ጋር አሲረዋል" በተባሉ ተከሳሾች ላይ ፍርድ ተሰጠ
Your browser doesn’t support HTML5
የአገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ ተቀዳሚ ወታደራዊ ችሎት “አገር ለማፍረስ ከህወሓት ጋር አሲረዋል” ባላቸው 48 ተከሳሾች ላይ ዛሬ ፍርድ ሰጥቷል።
ከነሃሴ 20/2013 ዓ.ም. ጀምሮ እያስቻለ ያለው ወታደራዊው ችሎት የዛሬዎቹን ጨምሮ በ154 ተከሳሾች ላይ ከሁለት ዓመት እስከ 18 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እሥራት ፈርዷል።