ባይደን የአፍጋኒስታኑ ጥቃት ዋጋ ያስከፍላል አሉ
Your browser doesn’t support HTML5
በአፍጋኒስታን ካቡል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ 13 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ሃይሎች እና ከ90 በላይ አፍጋንስታናዊያን ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ይሄንን ጥቃት ለፈጸማችሁ እና አሜሪካንን ለመጉዳት ምኞት ያላችሁ ሰዎች፣ ይህንን ተረዱት ይቅር አንላችሁም!” ሲሉ አጥቂዎቹን ዋጋ እንደሚያስከፍሏቸው ቃል ገብተዋል፡፡