የክረምቱ ዝናብ በኢትዮጵያ አደጋዎች ደቅኗል

Your browser doesn’t support HTML5

የክረምቱ ዝናብ በተለያዩ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች አደጋዎችን ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል። በአዋሽ፣ በአባይ ተፋሰስ እና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አካባቢዎች፣ በምዕራብ እና በመካከለኛ ኦሮምያ፣ በምዕራብ አማራና የደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በሚቀጥሉት 10 ቀናት ከባድ እና ነጓድጓዳማ ዝናብ እንደሚጠበቅ ኤጀንሲው አመልክቷል። ኅብረተሰቡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።