የድሬዳዋ አስተዳደር 3መቶ መደብሮችንና 13 መጋዘኖችን መዝጋቱን አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የድሬዳዋ አስተዳደር በምግብ ውጤቶች ላይ ያላግባብ ዋጋ ጨምረው እየሸጡ ነው ያላቸውን 300 ገደማ መደብሮችንና 13 መጋዘኖችን መዝጋቱን አስታወቀ። አስተዳደሩ ከአምራቾች፣ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የፊታችን ሰኞ በተወሰኑ የምግብ ነክ ምርቶች ላይ ተመጣጣኝ ነው የተባለ ዋጋ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። የፌደራሉ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን የሐምሌ ወር የምግብ ነክ ውጤቶች ዋጋ በ24 በመቶ ገደማ እንዳሻቀበ አመልክቷል።