በጸጥታ ሥጋት ከወልዲያ ከተማ የሸሹ ወደ ቀያቸው ተመለሱ

Your browser doesn’t support HTML5

ከወልዲያ ከተማ በጸጥታ ሥጋት ወጥተው የነበሩ ኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ፡፡
ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ቆይታ የነበራቸው ከንቲባው የሥጋቱ ምንጭ በማኅበራዊ የትስስር ገጾች የሚተላለፉ የሀሰት መልእክቶችና ፕሮፓጋንዳዎች ናቸው ብለዋል፡፡
የተወሰኑ የከተማዋ ኗሪዎች ከቀናት በፊት ወደ አጎራባች ከተሞች ሸሽተው መሄዳቸው የተነገረ ሲሆን ይህ ደግሞ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ያስከተለው ተጽእኖ እንደሆነ ነው ከንቲባው በተለይ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ያስረዱት፡፡