"የፓርኪንሰን ችግር ሰፊ ቢሆንም ስራችንን ከአዲስ አበባ ውጪ እንዳናስፋፋ የበጀት ችግር አለብን" ክብራ ከበደ
Your browser doesn’t support HTML5
የፓርኪንሰን ሕሙማን ድጋፍ ማኅበር በኢትዮጵያ ከተመሰረተ አስራ ሁለት ዓመት ይሆነዋል፡፡ የድርጅቱ መስራች ክብራ ከበደ ትሰኛለች፡፡ ማኅበሩ ከተመሰረተ ጀመሮ በበሽታው ዙሪያ ግንዛቤን ለመፍጠር የእግር ጉዞዎች፣ የውይይት ምሽቶች፣ የምክር አገልግሎቶች የሚሰጥ ሲሆን ለሕሙማኑም የምክር፣ የገንዘብ እና የሕክምና ድጋፍ እንዲያገኙ በማመቻቸት እየሰራ ይገኛል፡፡