ከነጻነት በኋላ የመጣው የደቡብ ሱዳን የአስር ዓመቱ መከራ
Your browser doesn’t support HTML5
ደቡብ ሱዳን የ10ኛ ዓመት የነጻነት ቀን በዓሏን ለማክበር እየተዘጋጀች ባለችበት ሰዓት የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት ፈንድ ዩኒሴፍ በሃገሪቱ ከሶስት ሕጻናት ሁለቱ ዓለም አቀፍ እርዳታ ይሻሉ ሲል ሃገሪቱን ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ እንደተጋረጠባት አስታውቋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት 1.6 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በሃገር ውስጥ መፈናቀላቸውን እና ሌሎች 2.2 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ ድንበር ተሻግረው በስደት እንደሚኖሩ ያሳያል፡፡