ቆሻሻን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ፣ የአንድ ኢትዮጵያዊ ተቋም ጉዞ

.

ከተለያዩ ክፍለ ከተሞቿ በሚወጣው የቆሻሻ ክምችት ምክንያት ስትፈተን የቆየችው አዲስ አበባ በተያያዥ ችግሮች ምክንያት የበርካታ ዜጎቿን ህይወት አጥታለች።በቆሻሻው ሰበብ በሚፈጠሩ ተላላፊ በሽታዎች ለህመም እና ከሚዳረጉት በተጨማሪ በድንገተኛ ተያያዥ አደጋ ምክንያት በአጭሩ የቀሩ ጥቂት አይደሉም። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በከተማዋ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በደረሰ የቆሻሻ ቁልል መደርመስ አደጋ ከ100 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች መርገፋቸው ነው።

ያ ዘግናኝ ክስተት የተፈጠረው የዛሬ አራት ዓመት ገደማ ነው። ዛሬ የእኒያ ኢትዮጵያዊያን ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ ያለፈበት ስፍራ በበጎ የሚነሱ እንቅስቃሴዎች እያስተናገደ እንደሆነ ይሰማል ። ከእነዚህ መካከል አንዱ ካምብሪጅ ኢንደስትሪስ የተሰኘው ተቋም የሚያንቀሳቅሰው የረጲ የቆሻሻ ማብለያ እና የኃይል ማመንጫ ተቋም ነው።

በቅርቡ በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ተቋም ከ2021 የቴክኖሎጂው ዓለም ፈር ቀዳጆች መካከል አንዱ ተደርጎ ዕውቅና የተሰጠው ተቋሙ በአንድ ዓመት ብቻ 530 ሚሊዬን ኪሎግራም ቆሻሻ ማስወገዱን ፣191 ሚሊዬን ኪሎዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋት እንዳስገባ የተቋሙ የቦርድ ሊቀመንበር እና ከመስራቾች መካከል አንዱ የሆኑት ሳሙኤል ዓለማየሁ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

አቶ ሳሙኤል ከባልደረባችን ሀብታሙ ስዩም ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ስለ ተቋሙ ጉዞ እና የመጪ ዘመን ዕቅዶች አጫውተውታል። አስቀድመው ስለ ራሳቸው እና ስለ ተቋሙ ጅምር ይነግሩናል ።

መሰናዶውን እንድታዳምጡ እንጋብዛለን።

Your browser doesn’t support HTML5

ምጥን ቆይታ ፡ -ቆሻሻን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ስለቀየረው ኢትዮጵያዊ ተቋም