ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ያደረጉትን ጥረት የሦስት ክልሎች ተወካዮች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮምያ የሲዳማ እና የደቡብ ክልሎች ክልሎቹ በሚዋሰንባቸው አከባቢዎች የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት በመስራታቸው ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን የክልሎቹ የፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ባለሥልጣናት ተናገሩ። በቀጣይም ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ለዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት በጋራ እንደሚሰሩ ከሦስቱም ክልሎች ፀጥታ አመራሮች እና ከሁሉም የፀጥታ ዘርፍ ተወካዮች ጋር በሃዋሳ ከተማ በመከሩበት ወቅት አስረድተዋል።