ጤፍ ለቆዳ ውበት መጠበቂያ? ቆይታ ከመድሃኒት ቅመማ ባለሙያዋ ህይወት ዮሃንስ ጋር

.

.

በሙያዋ ምክንያት የተለያዩ ሀገራትን ተዘዋውሮ ለማየት ዕድል ላገኘችው ህይወት ዮሃንስ ለጥቁር እና ጠይም ቆዳ የሚሆኑ ጤናማ የውበት መጠበቂያ ምርቶችን ማግኘት ፈተና ሆኖባት ቆይቷል። የኃላ ኃላ የተመረቀችበትን የመድሃኒት ቅመማ ዘርፍ ከትውልድ ሀገሯ ኢትዮጵያ ሀገራዊ አሻራዎች ጋር አስተባብራ በዐይነቱ ለየት ያለ የውበት መጠበቂያ አምራች ድርጅት መስራች ሆናለች።

ህይወት የመሰረተችው ድርጅት አስካላይት ፎርሚዩላ ይባላል። ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራት ቆይታ እንዳስረዳችው የዛሬ አራት ዓመት ገደማ የተቋቋመው ድርጅት ተፈጥሯዊ የሆኑ የውበት መጠበቂያ ምርቶችን እያቀረበ ይገኛል።

በቅርቡ ደግሞ በዘርፉ የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ከጤፍ የሚገኙ ንጥረነገሮችን በግብዓትነት የሚጠቀም የቆዳ ውበት መጠበቂያ እንዳመረተም ታክላለች።

አስካላይት ፎርሚዩላ ከምርቶቹ መጠሪያ ጀምሮ ሳይቀር የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካን አሻራ ላለመልቀቅ የሚጥር ዓይነት ነው። የአስራ ሶስት ወር ጸጋ፣ አዲስ ፣ፓን አፍሪካ ፣ጣና እና ጣእቱ የሚባሉ ምርቶችን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። ሁሉም ተገቢውን የምርት ጥራት እና ቁጥጥር ሂደት አልፈው ለገበያ መሰራጨታቸውን ህይወት ትናገራለች።

ለመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት የተጠቀሙበት ጤፍ በምን ሁኔታ ለውበት መጠበቂያነት ዋለ?ሀብታሙ ስዩም ይሄንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን ለህይወት ዮሃንስ አቅርቧል። ሙሉ መሰናዶውን ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ከጤፍ ስለተሰራው የቆዳ ውበት መጠበቂያ