ከ25 ዓመታት የአርት ስኩል ሞዴልነት ወደ ሰዓሊነት የመጣችው የሁለት ልጆች እናት- ፍቅርተ አያና

Your browser doesn’t support HTML5

ፍቅርተ አያና ላለፉት 25 ዓመታት በአለፈለገ ሰላም የስነጥበብ ትምህርት ቤት አርት ስኩል ውስጥ በአካለ ተምሳሌት ሞዴልነት ክረምት ከበጋ ሳትል ለረዥም ሰዓት ያህል በአንድ ዓይነት ቅርጽ አንድ ቦታ ላይ ብቻ አተኩራ በማየት እድሜዋን አሳልፋለች፡፡የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ፍቅርተን በመሳል እጅግ ብዙ ታዋቂ ሰዓሊያን እጃቸውን አፍታተዋል፡፡ፍቅርተ አሁን ላይ ስዕል መሳል ጀምራለች፡፡ ይሁንና ደሞዟ ለቀለም፣ ለቡሩሽ እና ለሸራ የሚበቃ ባለመሆኑ ድጋፍ ያስፈለገኛል ትላለች፡፡