በተቋሟ የሚሰሩ ሴቶችን የምታበቃው የተፈጥሮ የውበት መጠበቂያ አምራቿ ወጣት

Your browser doesn’t support HTML5

ዮርዳኖስ ጉሽ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት የተማረች ሲሆን በተለያዩ የብሮድካስት እና የህትመት ሚዲያዎች ላይም ሰርታለች፡፡ በአሁን ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያን ስኪን ቢውቲ ሲክሪትስ የተሰኘ የተፈጥሮ የቁንጅና ግብዓቶች የሚያመርት ተቋም ከፍታለች፡፡ ዮርዳኖስ ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አብረዋት የሚሰሩ 12 ሰራተኞቿ የራሳቸውን ሱቅ ከፍተው እንዲወጡ በማድረግም ሴቶችን ማብቃት ላይ የራሷን ሚና እየተጫወተች ትገኛለች፡፡