የመራጮች ምዝገባ መጓተትና የምርጫ ቦርድ ምላሽ
Your browser doesn’t support HTML5
የስድስተኛው ብሄራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች እስካሁን ያልተጀመረው በትራንስፖርት እጥረት ነው ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። በትናንትናው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም በየምርጫ ጣቢያዎቹ የመመዝገቢያ ስፍራ ቢዘጋጅም ምዝገባው ባለመጀመሩ ግን ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር።