በሶማሌ ክልል የእሥር ቤቶች ይዞታ እንዲሻሻል የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሶማሌ ክልል በታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች አያያዝ ላይ ጥሩ መሻሻሎች ያሳዬ ቢሆንም አሁንም ሊስተካከሉ የሚገቡ ጉዳዮች አሉ ብሏል። የማረሚያ ቤቶችና ማቆያዎች መጨናነቅ እንዲሁም ታዳጊዎች ከአዋቂዎች ጋር መታሰራቸውን በዋና ክፍተትነት ጠቅሶታል መግለጫው። ይሁንና የአሁኑ አያያዝ ቀድሞ ጄል ኦጋዴን ተብሎ ይታወቅ ከነበረው የማረሚያ ቤት አያያዝ ጋር የሚነጻጸር አይደለም ብሏል።