የህዳሴ ድርድር ኪንሻ ላይ ተጀመረ

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች አዲስ ድርድር ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ውስጥ ትናንት ጀምሯል። ድርድሩ እየተካሄደ ያለው በአፍሪካ ህብረት ጥላ ሥር ሲሆን የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር የኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ-አንቷን ችሴኬዲ ናቸው።