ከቀርክሃ እንጨት ካልሲ እና ምንጣፎች የምታመርተው ወጣት ይዲዲያ ዳምጠው

Your browser doesn’t support HTML5

ይዲዲያ ዳምጠው ወጣት ስራ ፈጣሪ ስትሆን አክሊል የተሰኘ ተቋም መስራች ናት፡፡ ከተመሰረተ ሁለት ዓመት እድሜ ያለው አክሊል በዋናነት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ለማምጣት የሚጥር ተቋም ሲሆን ከቀርክሃ እንጨት ክር በማምረት የመጀመሪያ ምርቱ የሆነው ሳባ ካልሲ በማምረት ስራውን ጀምሯል፡፡ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥም ልዩ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ንድፍ የያዙ ምንጣፎች እና ብርድልብሶችን ከቀርክሃ እያመረተ ይገኛል፡፡