በአማራ ክልል በሦስት ዞኖች ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖች ላይ ጉዳት ደረሰ
Your browser doesn’t support HTML5
በአማራ ክልል በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ በሦስት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖች ላይ ሰደድ እሳት አደጋ መከሰቱን የክልሉ ደንና ዱር እንስሳት ባለሥልጣን አስታውቋል። በአደጋው ከ1100 ሄክታር በላይ ጥብቅ ደን ጉዳት ደርሶበታል። ባለሥልጣኑ የአደጋው መንስዔ እየተመረመረ ቢሆንም ሰው ሰራሽ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።