በፍ/ቤት ትዕዛዝ አለመከበር አቤቱታ ላይ የኦሮምያ የጸጥታ ኃላፊ ምላሽ

Your browser doesn’t support HTML5

በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አይከበርም በሚል ለሚቀርቡ ወቀሳዎች ምላሽ የሰጡት የኦሮምያ ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ጅብሪል መሃመድ ምክንያቶቹን በቅርበት መመርመር እንደሚገባ ጠቁመዋል። አንድ ተጠሪጣሪ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት ቢቀርብና ባንዱ ነፃ ቢባልም ፖሊስ ግን የተጠረጠረበትን ሌላ ወንጀል እስኪያጣራ ድረስ ግለሰቡን ከእስር ላይፈታ እና መርመራውን ሊቅጥል ይችላል ብለዋል።