ከአንድ እስከ 8 ዓመት እድሜ ያሉ ሕጻናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩ መጽሃፍትን የማሰባሰብ እና ማዕከል መክፈት መርሃግብር

Your browser doesn’t support HTML5

የነገ ተስፋ ሕጻናት ለአዲስ አበባ፤ የተሰኘው መርሃግብር በአ.አ አስተዳደር የህጻናት ቀዳማዊ ልጅነት መርሃግብር በኩል በ 10 ክፍለከተማዎች ከአንድ እስከ ስምንት ዓመት እድሜ ላሉ ሕጻናት የሚያገለግል የመጽሃፍት ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ቢሮው በጎፍቃደኞች በዚህ የእድሜ ክልል ላሉ ሕጻናት የሚያገለግሉ መጽሃፍትን እንዲለግሱም ጥሪ አድርጓል፡፡ የመርሃግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ታቦር ገብረመድህን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡