የምርጫ ካርታ ውዝግብ - ሶማሌ እና አፋር

Your browser doesn’t support HTML5

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የአፋር ክልል ቅሬታ ባቀረበባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ምርጫ እንዳይካሄድ መወሰኑን እንደሚቃወም የሶማሌ ክልል መንግሥት አስታወቀ። የክልሉ መንግሥት አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ ካልተወሰደ ከምርጫው ራሱን እስከማግለል የደረሰ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችልም አስታውቋል። ከብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።