ኤርትራ ውስጥ በኮቪድ የተቋረጠው ትምህርት ሊጀምር ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ኤርትራ ውስጥ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመግታት በተወሰደው እርምጃ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በሚመጣው ሣምንት እንደሚጀመር የኤርትራ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ትምህርት መጀመሩ የወረርሽኙ ስጋት ቀንሷል ማለት እንዳልሆነ የገለፀው የትምህርት ሚኒስቴር ሲዘወተሩ የነበሩ የኮቪድ-19 መክላከያ መንገዶች መተግበር እንዳለባቸው አጥብቆ አሳስቧል።