በየጊዜው የሚደረጉ የጽዋ፣ ጀማ እና የጸሎት መርሃግብሮች ሴቶችን ለማብቃት ምን ሚና አላቸው?

Your browser doesn’t support HTML5

ከ160 ዓመት በፊት በጉራጌ ዞን እንደኖረች እና ለሴቶች መብት መከበር ትታገል እንደነበር በሚነገርላት በቃቄ ውርድወት ስም የተሰየመው መብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማሕበር(CARD) የሚያዘጋጀው 'ውርድወት የምርምር መርሃግብር' ወይም ፌሎውሺፕ የመጀመሪያ ምርምር ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ጥናቱ በየጊዜው በሴቶች የሚደረጉ የጽዋ ፣ ጀማ እና የጸሎት ቡድኖች በሴቷ ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያ ሕይወት ዙሪያ ያላቸውን ሚና ላይ ያተኮረ ነው፡፡