የኮቪድ ሥርጭት መባባስ እና የህብረተሰቡ ጥንቃቄ በኢትዮጵያ
Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ በኅብረተሰቡ ዘንድ እየታየ ያለው መዘናጋት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ሊያባብሰው ስለሚችል ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የጤና ባለሞያዎች እየመከሩ ነው። የጉደር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሕክምና ክፍል ኃላፊና የማዕከሉ ኮቪድ-19 ሕክምና አስተባባሪ ዶ/ር ናሆም ተሾመ፤ እርሳቸው በሚሠሩበት ሆስፒታል ውስጥ የታማሚዎች ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል።