ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት በኢትዮጵያዊያን ሞት የሁቲ ታጣቂዎችን ወቀሰ

Your browser doesn’t support HTML5

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂውማን ራይትስ ወች ባለፈው ሳምንት እሁድ በየመን ሰነዓ በፍለስተኞች ማቆያ ለሞቱት ኢትዮጵያዊያ ዜጎች የሁቲ አማጽያን ቡድንን ወቅሷል። ድርጅቱ ትላንት ባወጣዉ መግለጫ በአካባቢዉ የሚንቀሳቀሱ የሁቲ አማጽያን ያደረሱት ጥቃት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዲመረመር ጠይቋል።