የሳይንስ ትምህርቶች አጋዥ ልዩ የምልክት ቋንቋ መዝገበ ቃላት ይፋ ሆነ

.

የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶችን የመስማት እክል ለገጠማቸው ኢትዮጵያዊያን ለማስተማር ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የተነገረለት ልዩ የምልክት ቋንቋ መዝገበ ቃላት ከሰሞኑ ይፋ ተደርጓል።

መዝገበ ቃላቱ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን ስር በሚገኘው የሆሳዕና መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ነው። የፊንላንድ መንግስት ደግሞ የገንዘብ ድጋፍ እንዳደረገለት ተሰምቷል።

መዝገበ ቃላቱን የማሰናዳት ሂደቱን የመሩት ከሶስት ዓመታት በፊት የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊው ዶ/ር መኮነን ሙላት ናቸው። ስለመዝገበ ቃላቱ ይዘትና ፋይዳ የበለጠ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም በስልክ መስመር አነጋግሯቸዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

የሳይንስ ትምህርቶችን አጋዥ የምልክት ቋንቋ መዝገበ ቃላት ይፋ ሆነ