"ኮቪድ ሲመጣ የምንበላው ስላልነበረን አግብቻለሁ" የ17 ዓመት ወጣት

Your browser doesn’t support HTML5

ሃብታም በአማራ ክልል በጎንደር ትክል ድንጋይ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ ከኮቪድ 19 በፊት እናቷ ቤት ተከራይታላት ትምህርቷን ትከታተል ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት ኮቪድ 19 ሲገባ ስራ በመጥፋቱ ምክንያት ቀድሞም ቢሆን እዚህ ግባ የማይባለው የእናቷ ድጎማ ጭራሹን ቆመ፡፡ "እናቴ እስከመቼ እንዲህ ትኖራለች? ኮቪድ ሲመጣ ስራ ቆም እንጂ ሆድ እህል መጠየቁን አያቆም ብዬ ለትዳር ስጠየቅ አይኔን አላሸሁም” ትላለች፡፡