የአረና መግለጫ እና የአማራ ክልል ምላሽ
Your browser doesn’t support HTML5
በትግራይ ክልል በአሁኑ ሰዓት ያለውን የፀጥታ ችግር በአስቸኳይ በመቅረፍ ለሁሉም ተጎጂዎች የዕለት ደራሽምግብ እንዲያገኙ መደረግ እንዳለበት ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አሳሰበ። በትግራይ ክልል ያለውየሰብዓዊ ቀውስ እጅግ አሳሳቢ የገለፀው ፓርቲው፤ግድያ፣ዘረፋ በሴቶች ላይ የደረሰው ወሲባዊ ጥቃት፣መፈናቀል እና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የግዝፈታቸውን ያህል አለመነገራቸውን ገልፆ ሁኔታዎቹበአስቸኳይ እልባት ሊያገኙ ይገባል ብሏል።