ከግብርና ተረፈምርቶች የሚሰራ የወረቀት ጥቅል ፋብሪካ በማቆም ላይ ያለችው ወጣት

Your browser doesn’t support HTML5

ቤተልሄም ደጀኔ ለወረቀት አምራች ድርጅቶች የሚያገለግል ጥቅል ወይም ፐልፕ ሙሉ ለሙሉ ከግብርና ተረፈ ምርቶች የሚያመርት ዛፍሪ የተሰኘ ተቋም መስራች እና ስራአስኪያጅ ናት፡፡ ከ5 ዓመታት በፊት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የተመረቀችው ይቺ ወጣት በዋናነት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረቷን ያደረገች ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ከዛፍ ምርት ነጻ የሆነ እና በተጨማሪም ለአነስተኛ ገበሬዎች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሊሆን የሚችል ምርት ለማቅረብ ዝግጅቷን ጨርሳለች፡፡