ለሴቷ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ምጣኔ እና የሚኖረው ጠቀሜታ

Your browser doesn’t support HTML5

በአውሮፓዊያኑ 2021 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ተቋማት የቤተሰብ ምጣኔ 2020(ሃያ ሃያ) የዓለም አቀፍ የትብብር እና ተነሳሽነት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ 67 ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሃገራት ላይ የተሰራ ሲሆን ምንም እንኳን በድሃ ሃገራት ውስጥ ያለው የቤተሰብ ምጣኔ ተጠቃሚነት ቢጨምርም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ግን የቤተሰብ ምጣኔ እቅዱን በተገቢው መንገድ ለማስኬድ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረ አመላክቷል፡፡