"በጠመንጃ እና በሰላም አስከባሪ ታጅበን የሰላም ጉዞ አድርገናል ማለት አንችልም" ያሬድ ሹመቴ
Your browser doesn’t support HTML5
ከአዲስ አበባ ወደ አድዋ ሶሎዳ ተራራ የሚደረገው ጉዞ አድዋ ተጓዦች በዓሉን በአዲስ አበባ ለማክበር በጉዞ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ቀድሞ ይጓዙት ከነበረው ከ 1090 ኪ.ሜ ውስጥ ማሳካት የቻሉት 600 ኪ.ሜ ብቻ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በመነሻቸው ላይ ዓላማ ባደረጉት መሰረትም ህዝቡ መሃል በመግባት ያለውን መከራ እና ችግር መታዘባቸውን በመግለጽ ከብሽሽቅ ፖለቲካ ሊወጣ እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡