ኢትዮጵያዊያንን በኢንተርኔት የሚያሳትፍ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ዉድድር

Your browser doesn’t support HTML5

ተቀማጭነቱ በሰሜን አሜሪካ የሆነው ኢትዮ ግሎባል አርትስ ከያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር በመላዉ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት 'ዜማ ፍለጋ' የተሰኘ የድምጻዊነት ውድድር ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ውድድሩ በቨርችዋልና በአካል የሚካሄድ ሲሆን አሸናፊው አሜሪካን በሚገኘው ኢንትሪግ ሪከርድስ አልበሙን እንዲሰራና በተለያዪ የአሜሪካ ግዛቶች የኮንሰርት ስራዎች እንዲያቀርብ ግብዣ ይደረግለታል።