ኢሰመኮ በፍ/ቤቶች ትዕዛዝ አፈጻጸም ላይ

Your browser doesn’t support HTML5

ጅማ ውስጥ እሥር ላይ የሚገኘው የጅማ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮ ምሩቅ ሙሃመድ ዴክሲሶ “በአፋጣኝ ሊለቀቅ ይገባል” ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰመኮ/ አሳስቧል። ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ “ኦሮምያ ክልል ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የፍርድ ቤቶች ትዕዛዞች አለመከበራቸው አሁንም አሳሳቢ ነው” ብሏል።