መንግስት በግጭት ወቅት ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን እንዲከላከል የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ
Your browser doesn’t support HTML5
ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ህዝቦች ሃብት ንብረታቸውን በመተው ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ሴቶችም መደፈራቸው ተሰምቷል፡፡ ሴታዊት የጾታ ንቅናቄ በግጭት ቀጠና እና በሃገር ውስጥ የስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ለሴቶች ጥበቃ ቅድሚያ እንዲሰጥ እና ጥቃት ፈጻሚ አካላትም በተገቢው መንገድ ለህግ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡