የኢትዮጵያ ሕክምና መረጃዎች ማዕከላዊ በሆነ መንገድ እንዲሰነዱ የሚያግዘው ወጣት

Your browser doesn’t support HTML5

ኦርቢት ሄልዝ ከ4 ዓመታት በፊት በጳዚዮን ቸርነት የተቋቋመ የቴክኖሎጂ የጤና ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ስርዓት ማዕከላዊ በማድረግ የህሙማን መረጃ ሳይዘነጋና ሳይጠፋ እንዲሰነድ በተጨማሪም የታዘዙ መድሃኒቶች በተገቢው መልኩ እንዲከፋፍሉ በማድረግ ህሙማን በተለያዩ ህክምናዎች የሚያጠፏቸውን ጊዜና ገንዘብ እንዲሁም መጉላላት እንዲቀር እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡