በኮቪድ 19 ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሴት ተማሪዎች ወደ ት/ቤት እንዲመለሱ ልዩ ጥረት ያስፈልጋል ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

በማላላ ፈንድ አማካኝነት በኢትዮጵያ የትምህርት ሻምፒዮኖች በኩል የተሰራው እና ከ 1300 በላይ ቤተሰቦች የተሳተፉበት ጥናት ባለፈው ሳምንት ይፋ ሆኗል፡፡ በጥናቱ መሰረትም በኮቪድ 19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በድጋሚ በተከፈተበት በአሁን ሰዓት በሃገር ዓቀፍ ደረጃ ልጃገረዶች ላይ ያተኮረ እና ወደ ትምህርት ገበታቸው ሙሉ ለሙሉ እንዲመለሱ የሚያበረታታ አካሄድ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡