'የአሁኑን እየከተቡ የኋላውን መዘከር' ጥቂት ከፎቶግራፍ ባለሞያ መክብብ ታደሰ ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

መክብብ ታደሰ ወጣት የፎቶግራፍ ባለሞያ ሲሆን በተጨማሪም 'ጉጉት' የተሰኘ በድረገጽ ላይ በነጻ የሚሰራጭ ወጣት የፈጠራ እና የጥበብ ባለሞያዎች የሚዘከሩበት መጽሄት አጋር መስራች ነው፡፡ መክብብ በልጅነቱ አባቱ የስነ ሕንጻ ባለሞያ እንዲሆንላቸው ብለው ያስጀመሩት የስዕል ትምህርት አሁን ላለበት የፎቶግራፍ ስራ እንደገፋፋው ይናገራል፡፡