"ሴቶች በመንግስት የልማት ተቋማት ቦርድ ውስጥ ሃምሳ በመቶ መቀመጫ እንዲያገኙ እየሰራን ነው፡፡" ናሁሰናይ ግርማ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ጽኑ ሴቶች ማኅበር (ኤውብ) ከ10 ዓመት በፊት በናሁሰናይ ግርማ እና በሮማን ክፍሌ አማካኝነት በጥምረት የተመሰረተ ሲሆን፤ ባለፈው አስር ዓመት ጊዜ ውስጥም እጅግ ብዙ ሴቶች የቋንቋ፣ የንግድ ክህሎት እንዲሁም የተለያዩ ስልጠናዎች የሚያገኙበት፣ ትስስር የሚያደርጉበት፣ በስራቸው የበቁ እና የላቁ ሴቶች እውቅና እና ድጋፍ የሚያገኙበት እንዲሁም በፖሊሲ ደረጃ ተጽእኖ የሚያሳድሩበት ሆኗል፡፡