ወደ ስልሳ የሚጠጉ የታሪክ ምሁራን ማኅበር ለማቋቋም ተነሱ

Your browser doesn’t support HTML5

ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ምሁራን በኢትዮጵያ ሰላም ሚኒስተር እና በዴስቲኒ ኢትዮጵያ አማካኝነት ለአራት ቀናት ተሰባስበው ታሪክን ከግጭት እና ከሃሰት ትርክቶች በጸዳ ሁኔታ በሳይንሳዊ መንገድ ለመጻፍ ምን መደረግ እንዳለበት መክረዋል፡፡ በተጨማሪም ምሁራኑ ፖለቲከኞች በታሪክ ትምሕርት ላይ የሚያሳድሩትን ጫና ለማስተካከልና በታሪክ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመፍታት የታሪክ ምሁራን ማኅበር ለማቋቋም ወስኖ ኮሚቴ መስርቷል፡፡