የፈንድቃ የባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ የኔዘርላድ ፕሪንስ ክላውስ ሎሬት ተሸላሚ ሆነ

Your browser doesn’t support HTML5

ከጎዳና ሕይወት በመነሳት ከታዳሚዎች በሚያገኛት የሽልማት ገንዘብ ትምህርቱን የተማረው እና ሕይወቱን የቀየረው የባህል ተወዛዋዡ መላኩ በላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ የጀመረባትን የፈንድቃ የባህል ምሽት ቤት ከአምስት ዓመታት በፊት ገዝቶ ወደ ባህል ማዕከልነት ማሻገር የቻለ ወጣት ነው፡፡ በቅርቡም መላኩ በፈንድቃ የባሕል ማዕከል ለሚሰራቸው ስራዎች የኔዘርላንድስ የዘውድ ሽልማት የሆነው የፕሪንስ ክላውስ 2020 ሎሬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡