በጣልያን ስኬታማዎ ትውልደ-ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሞተው ተገኙ።

Your browser doesn’t support HTML5

በጣልያን ሰሜን ትሬንቲኖ ግዛት በከፈቱት ስኬታማ የእንሳት እርባታ እና የአይብ መደብር ትኩረትን ስበው የነበሩት ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ አጊቱ ጉደታ በቤታቸው ሞተው መገኘታቸው ተሰምቷል። የጣልያን ፖሊስን ዋቢ ያደረጉ መገናኛ ብዙሀን አጊቱ በሰው እጅ ህይወታቸው ሳይጠፋ እንዳልቀረ አስታውቀዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን እየተከታተለው እና የምርመራ ውጤቱን ከፖሊስ እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል። ሀብታሙ ስዩም ዝርዝር ዘገባ አለው።