ወጣት ሴቶችን ከበቁ ሴቶች ጋር በማጣመር ለአመራር የሚያበቃ መርሃግብር
Your browser doesn’t support HTML5
የዩንቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን ለማብቃትና ስኬታማ ለማድረግ፤ የበቁ ሴቶችን ከወጣት ሴት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ጋር የማጣመር መርሃግብርን ማስጀምሩን የሴቶች ሕጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ መርሃግብሩ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ተቋም UNWOMEN እና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የሚተገበር መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አድነው አበራ ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቀዋል፡፡