በጽኑ የታመሙ ሕጻናትን ዕለት ዕለት በፈገግታ የሚያክመው ፍካት የሰርከስ ቡድን
Your browser doesn’t support HTML5
ከተመሰረተ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው ፍካት ሰርከስ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሰርክስ ፌስቲቫል አዘጋጅ ነው፡፡ በተጨማሪም ቡድኑ ‘የፈገግታ መድሃኒት’ የሚል መርሃግብር ቀርጾ በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሕጻናት ልዩ ክፍል በሳምንት 6 ቀናት ሕጻናቱ በማዝናናት ያስተምራል፡፡ ኤደን ገረመው ከቡድኑ መስራቾች አንዱ የሆነውን የቡድኑን የፈጠራ ዳይሬክተር ደረጀ ዳኜ አነጋግራ ተከታዩን አዘጋጅታልናለች፡፡