ኢትዮጵያዊው የማር ወይን ነጋዴ የ750 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆነ

Your browser doesn’t support HTML5

በካሊፎርኒያ ሶኖማ ግዛት የሚኖረው አየለ ሰለሞን የጠጅ ባህል በማጥናት የጠጅ ጣዕም እና ሽታ ያለው የማር ወይን መጥመቅ ችሏል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታትም ቢ ዲቫይን የተሰኘውን የማር ጠጅ በመሸጥ እና በዓለም ዙሪያ በማስተዋወቅ ላይ ቆይቷል፡፡ የኮቪድ 19 ወረሽኝ ከፍተኛ ወደሆነ ኪሳራ እና የገበያ መቀስዛቀዝ ያደረሰበት ሲሆን ይህን ችግሩን ለመቅረፍም በአሜሪካ ግዙፉ በሆነው የንግድ ውድድር ሻርክ ታንክ ውስጥ በምሳተፍ 750,000 ዶላር አሸናፊ ሆኗል፡፡