ከኢትዮጵያ የተሰረቁ ቅርሶችን ተከታትሎ የሚያስመልስ ኮሚቴ ተቋቋመ

Your browser doesn’t support HTML5

ከኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የተዘረፉ ቅርሶችን የሚያስመልስ አስራዘጠኝ ታዋቂ እና ተጽእኖም ፈጣሪ ሰዎች የተካተቱበት ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡ ኮሚቴው በዓለም ዙሪያ ያሉ የሃገሪቱን ቅርሶችን በማጥናት ከሃገራት ጋር በስምምነት እና በመግባባት ዓለም ዓቀፍ የቅርስ ጥበቃ ሕግን ባከበረ መልኩ ለመስራት ዓላማ እንዳለው የኢትዮጵያ የባህል እና የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡