በቀን ከአራት ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሱዳንን ድንበር እየተሻገሩ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዩኤን ኤች ሲ አር ሱዳን ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ በቀን ከ4000 በላይ ኢትዮጵያን ስደተኞችን እየቀበለ መሆኑን እና አስታወቀ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በትግራይ ክልል ባለው የመሰረታዊ ዕቃ አቅርቦት ችግር እና የእንቅስቃሴ ገደብ ሳቢያ ትልቅ ሰብዓዊ ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ኤደን ገረመው የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ሶፊያ ጄንሰንን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡