የፕ/ት ትራምፕን ንግግር የተቃወሙ ትውልደ- ኢትዮጵያዊያን ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያደረጉትን ንግግር በመቃወም ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ -ኢትዮጵያዊያን ከፕሬዚደንቱ መኖሪያ ስፍራ "ዋይት ኃውስ " ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። የፕሬዚደንቱ ንግግር የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት የሚሸክር እና ተገቢነት የሌለው ነው ሲሉም ተችተዋል።