"ኢትዮጵያ ጾታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን እስከ እድሜልክ ድረስ ተወቃሽ የሚያደርግ የምዝገባ ስርዓት ልትጀምር ነው"
Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ የጾታዊ ጥቃት ቁጥር ለመቀነስ በፍርድ ቤት ወንጀልኝነታቸው የተረጋገጡ ጥቃት አድራሾችን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ የሚመዝግብ እና ከተመረጡ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎች ለማግለል የሚረዳ የብሄራዊ የጾታዊ ጥቃት አድራሾች ምዝገባ ሊጀመር ነው ተባለ፡፡ኤደን ገረመው በሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬተር የሆኑት አቶ አድነው አበራን እና የኢትዮጵያን ሴቶች ማህበራት ንቅናቄ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገ/መድህንን አነጋራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡