ዩኒቨርስቲዎች ሲከፈቱ ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን ታሳቢ በማድረግ ለግቢ ጥበቃዎች በፌደራል ፖሊስ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ
Your browser doesn’t support HTML5
ለፈው ግማሽ ዓመት ተፈጥረው የነበሩ የተማሪዎች ግጭት እና የትምህርት መስተጓጎል ተሞክሮ በመነሳት እና መጪው የምርጫ ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ለግቢ ጥበቃ አባላት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚነሱ የብሄር እና የፖለቲካ ግጭቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስልጠና በሃገር አቀፍ ደረጃ መስጠት ጀምሯል፡፡