ኢትዮጵያውያን ለኮሮና ቫይረስ ያላቸው ምላሽ ምን እንደሚመስል እና አመጋገባቸው አግዟቸው እንደሆን የሚያጠና ጥናት ይፋ ሆነ

Your browser doesn’t support HTML5

የጤና ሚኒስተር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የምርምር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡ ኮቪድ 19 ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራቶች አንጻር በአፍሪካ እና በኢትዮጵያ ያለው ጉዳት እንዴት ሊቀንስ ቻለ? ባህላዊ ሕክምና? የዓየር ንብረት? አመጋገብ ወይስ ሌላ የሚለውን ጥናቱ እንደሚያካትት እና ከ6 ሺ በላይ ሰዎች ላይ እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስተር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገረዋል፡፡