የትውልደ - ኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን የተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ - ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወም ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ አካሄዱ። ሰልፈኞቹ ተቃውሞውን ያደረጉት መንግሥት በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ይደርሳል ያሉትን የመብት ረገጣዎች ለማጋለጥ እንደሆነ ገልፀዋል። ሰልፉን ያዘጋጁት በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ሲሆኑ፤ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ተሳታፊዎች እንዳሉበት ተናግረዋል።